Featured

First blog post

This is the post excerpt.

Advertisements

This is your very first post. Click the Edit link to modify or delete it, or start a new post. If you like, use this post to tell readers why you started this blog and what you plan to do with it.

post

ከራስ ለራስ የተፃፈ ማስታወሻ!
መናገርህ ከዝምታህ የበለጠ መልካምና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ተናገር!
አንድ ነገር ከሆነ በኃላ መፀፀቱ የፈሰሰን ውኃ እንደማፈስ ከንቱ ነገር ነው። ያለ አግባብ የሚወጣ ቃል ህይወትን ሙሉ ያበላሻል ታላቅንም ዋጋ ያስከፍላል። አዕምሮህ ላይ ብልጭ ያለውን ሁሉ አትናገር ፣ አትፃፍ ብልጭ ያለ ሁሉ ድርግም ማለቱ አይቀርም። በጥርስህ ልትፈታው የማትችለውን ችግር በምላስህና በብዕርህ አትተብትብ። ንግግርህን ቆጥብ ዝግ ብለህ በትኩረት አጢነህና አስበህ ተናገር አንድ ሺህ ግዜ ለካና አንድ ጊዜ ቁረጥ።
እውቀት በሌለህ ጉዳይ ላይ አትናገር!

አላህ እንዲህ ብሏል፦
” وَلاَ تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولـئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْؤُولاً ”
«ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል ፤ መስሚያ ማያም ልብም እነዚህ ሁሉ (ባለቤታቸው) ከነሱ (በአላህ) ተጠያቂ ነውና»

【አል–ኢስራእ :36】
መልካምን ተናገር ወይም ዝም በል!

ነብዩ ﷺ አንዲህ ብለዋል፦
“مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاَللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَصْمُت”
«በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል»
【አል ቡኻሪይ (6018) ፣ ሙስሊም (47) ዘግበውታል】
ስለማይመለከትህ አትናገር!

ነብዩ ﷺ አንዲህ ብለዋል፦
“مِنْ حُسْنِ إسْلَامِ الْمَرْءِ تَرْكُهُ مَا لَا يَعْنِيهِ”.
«የአንድ ሰው እስልምናው ማማሩ ምልክቱ የማይመለከተውን መተው ነው»
【ቲርሚዚይ (2318) ፣ ኢብኑ ማጃህ (3976) ዘግበውታል】
ልብ በል የፈለገውን የሚናገር ያልፈለገውን ይሰማል ይባላልም!
በተቆጣህና በጋልክ ቁጥር አትናገር አትፃፍ ። ቁጣህ የሚያስከትለውን ጦስ አስብ። የጋለ ሁሉ ምንም ጊዜው ቢረዝም መብረዱ አይቀርም የሚያሳዝነው በግለት ጊዜ ያቃጠለውንና ያቆሰልለውን አካል መልሼ ላክም ብንል ቁስሉ ቢድን እንኳን ጠባሳው ላይሽር ይባስ ብሎም እድሉም ላይገኝ ይችላል። ስለሆነም ወደፊት በፀፀት ታሞ ከመማቀቅ ዛሬ መጠንቀቅ ይበጃል። ቆም ብሎ በእርጋታ ማሰብ ግድ ይላል! የረጋ ወተት… በተናደድክ ጊዜ ዝም በማለትህ ከእድሜ ልክ ፀፀት ራስህን ታድናለህ።
አትቆጣ!
ቁጣ የድመትን ጀርባ ሲያጎብጥ እንጂ የማንንም ጉዳይ ሲያቀና አላየሁም!
“أَبِي هُرَيْرَةَ أَنْ رَجُلًا قَالَ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَوْصِنِي. قَالَ: لَا تَغْضَبْ، فَرَدَّدَ مِرَارًا، قَالَ: لَا تَغْضَبْ”
አቡ ሁረይራ ባወሩት ሐዲስ አን ሰው ወደ ነብዩ ﷺ በመምጣት ምከሩኝ አላቸው።

ነብዩም ﷺ “አትቆጣ” አሉት ። ሰዉየውም ደጋግሞ እንዲመክሩት ጠየቀ። እሳቸውም “አትቆጣ” አሉት።»
【አል ቡኻሪይ (6116) ዘግበውታል】
የምትናገረውም ሆነ የምትፅፈው የአኼራ የስራ መዝገብህ ላይ እንደሚፃፍ አትዘንጋ!
“مَا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ ”
«ከቃል ምንም አይናገርም (እያንዳንዱ የሰው ልጅ)፣ በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የሆኑ (መዝጋቢ መላዕክት) ያሉበት ቢሆን እንጂ»

【ቃፍ: 18】
የጀሀነም እሳትን መቋቋም እንደምትችል በራስህ ከተማመንክ ያሻህን ተናገር!

ነብዩ ﷺ ለሙዓዝ አንዲህ ብለውታል፦
“وَهَلْ يَكُبُّ النَّاسَ عَلَى وُجُوهِهِمْ -أَوْ قَالَ عَلَى مَنَاخِرِهِمْ- إلَّا حَصَائِدُ أَلْسِنَتِهِمْ؟!”
«ሰዎች በፊቶቻቸው ወይም በአፍጢማቸው እሳት ውስጥ የሚወረወሩት ምላሳቸው ባጨደችው አይደለምን?»
【ቲርሚዚይ (2616) ዘግበውታል ሐዲሱን ሐሰኑ ሰሒሕ ብለውታል ፣ ኢማሙ አልባኒ ሶሒሕ አል’ጃሚዕ (5136) ላይ ሰሒሕ ብለውታል】
ትንሽ ማስታወሻ ከነገ ብዙ ሀዘን ይበልጣልና ነው የከተብኩት።

ቆም ብለን ራሳችንን እንገምግም!
” فَسَتَذْكُرُونَ مَا أَقُولُ لَكُمْ وَأُفَوِّضُ أَمْرِي إِلَى اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ ”
«ወደ ፊትም ለናንተ የምላችሁን ምክር (ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሳላችሁ፤ ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ ፤ አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና»

【ጋፊር 44】

««ከፊትና ጋር የሄደው ቢሄድ!የጠመመው ቢጠም!የመጣው ቢመጣ ሀቅና የሀቅ ባለቤቶች ግን ይቀራሉወሊላሂል ሀምድ!!!»»ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን ሃፊዘሁሏህ